Mountain sun rising

ስለ እኛ

Education for Ethiopia (ትምህርት ለኢትዮጵያ) ቅርብ ጊዜ የተጀመረ የበጎ አድርጎት ኩባኒያ ነው። ኢትዮጵያውያን፥ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ወዳጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው የሚሰሩበት ኩባኒያ ሲሆን አላማውም በሚሊዮንዎች የሚቆጠሩ የተማሩ እና በራሳቸው የሚተማመኑ ዜጋዎችን ማፍራት ነው። 

ቡድናችን
ሊና ጌታቸው አየነው

ዳይሬክተር እና መስራች

​ሊና የድርጅቱ መስራች እና ዳይሬክተር ስትሆን አዲስ አበባ ውስጥ ነው ተውልዳ ያደገችው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዎችዋን አሜሪካ በሚገኘው ዬል ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ያጠናቀቀችው በአሁኑ ሰዓት በቻይና ሀገር በቤጂንግ ከተማ ነው የምትኖረው። 

​ክሌሞ ዦን

ዋና የቴክኒክ ኦፊሰር 

ክሌሞ ፈረንሳዊ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን በሀገሩ በሚገኝ ኤፒቴክ የተሰኘ ዩኒቨርሲቲ ነው ያገኘው። ሁለተኛ ዲግሪውን በቻይና ታዋቂ ከሆነው ቺንግኋ ዩኒቨርሲቲ በኮምፒውተር ሳይንስ አጠናቋል። በቻይና ሀገር በቤጂንግ ከተማ ነው የሚገኘው። 

​ቤዛ ኤርሚያስ ዳኜ

​የባዮሎጂ ቪዲዮ ሌክቸረር 

ቤዛ በ"ማስተርስ ኦፍ ኤዱኬሽን" ትምህርት ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሂውስተን የተመረቀች ሲሆን በቴክሳስ በሚገኙ ትምህርት ቤትዎች ውስጥ የ9ኛ እና የ8ኛ ባዮሎጂ መምህርት ሆና አገልግላለች። የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘችው ደግሞ በህንድ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፑኔ በ"ባዮቴክኖሎጂ" ትምህርት ነው። በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በ"ጄኔቲክ ኢንጂነሪንግ" እና በእፅዋት "ቲሹ ካልቸር" ብዙ ልምድን አካብታለች። 

​ቢልልኝ አማረ

​የፊዚክስ ቪዲዮ ሌክቸረር 

ቢልልኝ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኘው የሜካኒካል እና የኢንዱስትሪያል ኢንጂኒሪንግ ዲማርትመንት ሌክቸረር ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በራያ ቆቦ ተወልዶ እ.አ.አ. በ2015 የመጀመሪያ ዲግሪውን እና በ2017 የማስተርስ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኘ ሲሆን ያጠናውም ሜካኒካል ኢንጂኒሪንግ ነው። በበጣም ታልቅ ዲስቲንክሽን ተመርቆ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚሰጡ የፊዚክስ ትምህርትዎችን ከእ.አ.አ 2015 ጀምሮ ሌክቸር እያደረገ ይገኛል። 

​ምህረት ገረመው

​የሒሳብ ቪዲዮ ሌክቸረር 

ምህረት የኮንክሪት ማቴርያል እና ስትራክቸርስ ተመራማሪ ስትሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና የሁለተኛ ዲግሪዋን ተከታትላለች፡፡ በኢንደስትሪ እና በትምህርቱ ዘርፍ አስር ዓመት የሚጠጋ የስራ ልምድ ያላት ሲሆን ከሙያዊ ስራዋ በተጓዳኝ ማህበረሰብንና አካባቢን በተጨባጭ ሊጠቅሙ የሚችሉ ስራዎችን መስራት ላይ ታተኩራለች::

​ዘካሪያስ ተሾመ

​የሒሳብ ቪዲዮ ሌክቸረር 

​ዘካሪያስ

 
 
​አማካሪዎቻችን 
​ኔተን ስቶነር

​የቦርድ ቼርማን እና አማካሪ

​ሊና የድርጅቱ መስራች እና ዳይሬክተር ስትሆን አዲስ አበባ ውስጥ ነው ተውልዳ ያደገችው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዎችዋን አሜሪካ በሚገኘው ዬል ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ያጠናቀቀችው በአሁኑ ሰዓት በቻይና ሀገር በቤጂንግ ከተማ ነው የምትኖረው። 

ቢኒያም አሰፋ ጥበቡ

የትምህርት ጉዳዮች ላይ አማካሪ

ቢኒያም

© የ 2020 Education for Ethiopia መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።