የእኛ ምኞት የተማረች ኢትዮጵያን መገንባት ነው።
በኢትዮጵያ የሚገኙ ተማሪዎች ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲለውጡ መርዳት አላማችን ነው።
ትምህርት ለኢትዮጵያ (Education for Ethiopia) የበጎ አድርጎት ኩባንያ ሲሆን አላማውም የዲጂታል ትምህርትን ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማቅረብ ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋዎች እና ባህሎች ሀገር ናት። ከሀገሪቷ ህዝብዎች መካከል 40 ፐርሰንት ያህሉ ከ14 ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ ታዳጊዎች ናቸው። ህልማችን የኢትዮጵያ ተማሪዎች በራሳቸው ቋንቋዎች የተሰሩ የዲጂታል ትምህርት አጋዥዎችን በመጠቀም ራሳቸውን እና ሀገራቸውን እንዲለውጡ ማገዝ ነው።
የቋንቋ ችግር
የሳይንስ ትምህርትዎችን በደንብ በማንናገረው ቋንቋ መማር እጅግ ከባድ ነው።
የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ከሚያጋጥሟቸው ችግርዎች አንዱ የከፍተኛ ትምህርት የሚሰጠው በእንግሊዘኛ በመሆኑ እና ብዙዎቻቸው የእንግሊዘኛ ችሎታቸው ያን ያህል ባለመሆኑ ከባባድ የሆኑ የትምህርት አይነትዎችን (በተለይም ሒሳብ እና ሳይንስ ላይ የሚያተኩሩትን) በቀላሉ አለመረዳታቸው ነው። እኛ ይህን ከተማሪዎቹ እና ከትምህርት ቤት መካከል የሚፈጠረውን ክፍተት የመሙላት ተስፋ አለን። ትምህርት ቤትዎችን የመተካት ፍላጎትም ሆነ አቅም የለንም። ነገር ግን ተማሪዎችን በመደገፍ ትምህርቱ በቀላሉ እንዲገባቸው ማድረግ እንችላለን።
የጊዜ ችግር
ከትምህርት ውጪ ተማሪዎቻችን ብዙ ሐላፊነት አለባቸው።
አንዳንዴም ከእድሜአቸው በላይ የሆኑትን ሐላፊነትዎችን ተሸክመው ለትምህርት ያላቸው ጊዜ ጠባብ ይሆናል። እንደሚታወቀው እነዚህ ሐላፊነትዎች ሴትዎች ልጆች ላይ በተለይ ተፅዕኖ ያደርጋሉ።
-
እንጀራ መጋገር እና ለቤተሰቡ ምግብ ማብሰል
-
ገበያ ላይ ወጥቶ ለቤተሰቡ ገቢ ማስገኘት
-
ታናናሽ ወንድም እና እህትዎችን መንከባከብ
-
ኧረ ስንቱ!
የእኛ አስተዋፅኦ
የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ
የዲጂታል ትምህርትን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ከማቅረብም ባሻገር ተማሪዎች የሚያውቋቸው ምሳሌዎችን በመጠቀም ትምህርት እንዲቀላቸው እናደርጋለን።
የዲጂታል ትምህርታችን ተማሪዎች በራሳቸው ፍጥነት እንዲያጠኑና እንደፈለጉ እንዲደጋግሙ ይረዳቸዋል። በተለያዩ ምክንያትዎች ከትምህርት ገበታ ላይ ለትንሽ ጊዜ ቢነሱ እንኳን የኛ ፕሮግራም በቀላሉ ያካክሳቸዋል።
በተጨማሪም ትምህርታችን በቃላል ቪዲዮዎች የተቀናበረና በተለያዩ የታወቁ የትምህርት ተቋማት የተደገፈ ነው።
ተማሪዎች ግባቸውን እንዲመቱ ማድረግ።
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ተገቢው ድጋፍ ቢደረግላቸው ትልቅ ደረጃ ላይ ይደርሳሉ።
ኢትዮጵያ የወጣትዎች እና የታዳጊዎች ሀገር ናት። እነዚህ ወጣትዎች ከራሳቸውም አልፈው ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰባቸውን መርዳት ይችላሉ። ይህንን እውን ለማድረግ የእኛ ሚና ትምህርትን በቀላሉ ማቅረብ እና ምቹ ማድረግ ነው። ህልማችን የዛሪዎቹን ተማሪዎች ወደ ነገዎቹ ባለሞያዎች እና ፕሮፌሽናልዎች መለወጥ ነው።
አጋርዎቻችን
ከተለያዩ ተቋምዎች ጋር በመተባበር አላማችንን እውን ማድረግ
በአሁኑ ሰዓት ከታዋቂው ካን አካዳሚ "Khan Academy" ጋር ስምምነት አለን። የእነሱን ትምህርት ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የመለወጡን ስራ እያከናወንን እንገኛለን። ከሌሎች አጋርዎች ጋርም የመስራት ፍላጎት አለን። በተለይም በትምህርት ይዘት፥ ትርጉም እና ተደራሽነት ላይ አብረውን የሚሰሩ ድርጅትዎች እና ተቋማትን ሁሌም እንፈልጋለን። አንድ ላይ ሆነን በመተባበር የኢትዮጵያ ልጅዎች ላይ አውንታዊ ተፅዕኖ እንደምናሳድር ምንም ጥርጣሬ የለንም።
ማክሚላን ስትዋርት ፋውንዴሽንን ላደረገልን የግራንት ትብብር ከልብ ለማመስገን እንወዳለን።
ስቴምፓወር የተሰኘው የትምህርት ተቋም የሳይንስ፥ የሒሳብ እና የቴክኖሎጂ ትምህርትዎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን በአፍሪካ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ትልቅ አሻራ አለውው። በሀገሪቷ የሚገኙትን የሳይንስ ማዕከላትን በመጠቀም የትምህርት ግብዓትዎቻችንን በመላ ሀገሪቷ ለሚገኙ ተማሪዎች ተደራሽ እናደርጋለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትምህርትን እየደገፍን እንገኛለን። አላማችን ከትምህርት ቤትዎች ጋር መስራትና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዝግጅትዎች ላይ ተሳትፎ እና እገዛ ማድረግ ነው።
We are collaborating with China-based NGO, Shero League, in order to provide 1on1 Chinese learning for selected Ethiopian students. In this program, young college students and graduates from China provide intro Chinese lessons to young people in Ethiopia. Would you like to see a video showing the progress of students in just a few months?
Established in 1926, Lycée Guebre-Mariam is the most prominent French school in Ethiopia. We are honored that they are providing us access to their state-of-the-art laboratories to film our STEM content for a wider audience. Through this collaboration, we are hoping that millions of students who don't have access to the same facilities can still broaden their horizons.
ከብሎጋችን